ለጊዜያዊ የተጠበቀ ስታተስ ማመልከት

ለመኖርና ለመስራት ህጋዊ መብት የሌላቸው በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከዲሴምበር 12 ቀን 2022 እስከ ጁን 12 ቀን 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ጊዜያዊ የተጠበቀ ስታተስ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ። ፎርም I-821 በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም ፎርም I-765 በመጠቀም የስራ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

ለጊዜያዊ ጥበቃ ስታተስ ብቁ ለመሆን ከኦክቶበር 10 ቀን 2022 በፊት አሜሬካ መግባት እና ከዲሰምበር 12 ቀን 2022 ጀምሮ አሜሪካ ውስጥ በአካል መገኘት ማሳየት ይጠይቃል።

ጊዜያዊ የተጠበቀ ስታተስ ማግኘት ግሪን ካርድ ወይም የአሜሪካ ዜግነት አያስገኝም። የኢትዮጵያ ጊዚያዊ ጥበቃ ስታተስ ሲያበቃ ህጋዊ ስደተኛ ለመሆን የጀመሩት ሂደት ከሌለ ከአሜሪካ ሊባረሩ ይችላሉ።


Posted

in

by

Tags: