ወደ አሜሪካ መጓዝ የሚፈልጉ መንገደኞች በሙሉ ቪዛ ያስፈልጋቸዋል። ስደተኛ ቪዛ እዛ ለዘለቄታው መኖር ለሚፈልጉ ሰዎች ሲሆን ስደተኛ ያልሆነ ቪዛ ደግሞ ወደ አገራቸው ለመመለስ ላሰቡ ሰዎች ነው።
- የቪዛ ማመልከቻ ሂደቱ ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል ሂደቱን ቀደም ብሎ መጀመር ይመከራል።
- በተጨማሪም ቪዛ ሊከለከል ስለሚችል ጥብቅ የጉዞ እቅድ አያድርጉ።
- ቪዛው ያልተመታበት ምክንያት ከተፈታ እንደገና የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ከፍለው ለሌላ ቪዛ ማመልከት ይችላሉ።
- ቪዛው የተመታበት ፓስፖርት አገልግሎት ቀን ካለፈ አዲስ ፓስፖርት አውጥተው ሁለቱንም ፓስፖርት ይዘው መጓዝ የችላሉ።