የቪዛ ክፍያ ጭማሪዎች ሜይ 30, 2023 ላይ ሥራ ላይ ውለዋል። የንግድ ወይም የቱሪዝም የጎብኚዎች ቪዛ (B1/B2) እንዲሁም የተማሪዎችና የተለዋዋጭ ጎብኚዎች ቪዛ ክፍያ ከ$160 ወደ $185 ዶላር ጨምሯል። ለጊዜያዊ ሠራተኞች ስደተኛ ላልሆኑ ቪዛዎች (H, L, O, P, Q, እና R ምድቦች) ክፍያ ከ $ 190 ወደ $ 205 ዶላር ጨምሯል። በልዩ ሙያ (ኢ ምድብ) ውስጥ ለውል ነጋዴ፣ ለስምምነት ኢንቨስተርና ለስምምነት አመልካች የሚከፈለው ክፍያ ከ$205 ዶላር ወደ $315 ዶላር ጨምሯል።
በአሜሪካ ዜግነት እና የስደት አገልግሎት በ 2023 የበጋ ወራት አካባቢ የስደተኛ ማመልከቻዎች ክፍያ በሚከተለው መልኩ እንደሚጨምሩ ማቀዱን አሳውቋል።
ፎርም | ያሁን ክፍያ | የታቀደው ክፍያ | |
ለእጮኛ ቪዛ | I-129F | $535 | $720 |
የጋብቻ ቪዛ (CR-1) | I-130 | $535 | $820 |
የግሪንካርድ ኮንዲሽናል ሁናቴ ለማንሳት | I-751 | $680 | $1,195 |
ለስራ ፍቃድ ማመልከቻ | I-765 | $410 | $650 |
ያለቪዛ ለመጓዝ | I-131 | $575 | $630 |
የግሪን ካርድ ማመልከቻ (ከ 14 ዓመት በታች ከሆነ) | I-485 | $750 | $1,540 |
የአሜሪካ ዜግነት ማመልከቻ | N-400 | $640 | $760 |
የግሪን ካርድ ማመልከቻ | I-485 | $1,225 | $1,540 |
አስተያየት ለመጨመር መግባት አለብዎት።