የፎቶግራፍ መስፈርቶች
- ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የተነሱት ፎቶ
- በነጭ ባክግራውንድ ላይ
- ፊት ሙሉ በሙሉ መታየት አለበት
- በየዕለቱ የሚለብሱትን ልብስ ይልበሱ። ዩኒፎርም ለብሶ መነሳት አይፈቀድም።
- በሃይማኖት ምክንያት እና እለት እለት የሚያረጉት ካልሆነ በስተቀር ባርኔጣ ወይም ራስ መሸፈኛ አያድርጉ። ካረጉም ፊቶት ላይ ምንም ዓይነት ጥላ መጣል የለበትም።
- መነጽር አድርጎ ፎቶ መነሳት አይፈቀድም። መነጽር አድርገው ከተነሱ የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርቦታል። የሌንስ ፍሬም ወይም ነጸብራቅ ዓይኖትን ሊሸፍን አይገባም።
የታተመ ፎቶ
- የግድ 51 ሚሊ ሜትር በ 51 ሚሊ ሜትር መሆን አለበት
- ከራስ እስከ አገጭ በቁመት 25 ሚሊ ሜትር – 35 ሚሊ ሜትር መሆን ይኖርበታል
- የዓይን ቁመት (ከምስሉ ታች እስከ ዓይን ድረስ ሲለካ) ከ28 ሚሜ – 35 ሚሊ ሜትር መሆኑን ያረጋግጡ
ዲጂታል ፎቶ
- ፀጉሩን ጨምሮ ከራስ እስከ ታችኛው የአገጭ ክፍል ከ 50% እስከ 69% የምስሉ ጠቅላላ ቁመት መሆን አለበት።
- የዓይን ቁመት (ከምስሉ ታች እስከ ዓይን ድረስ ሲለካ) የምስሉ ቁመት ከ56% እስከ 69% መሆን ይኖርበታል።
- የምስል ፒክስል ስፋት በአንድ ካሬ ገጽታ ውስጥ መሆን አለበት (ማለት ቁመቱ ከስፋቱ ጋር እኩል መሆን አለበት ማለት ነው)። ከ 600 ፒክስል (ስፋት) x 600 ፒክስል (ቁመት) እስከ 1200 ፒክስል (ስፋት) x 1200 ፒክስል (ቁመት) ናቸው ተቀባይነት አለው።
- የፋይሉ መጠን 240 KB ወይም ከዚያ በታች መሆን አለበት።
- የፋይል ቅርጸት jpg ወይም jpeg እና በ SRGB ቀለም ቦታ መሆን አለበት።