የትምህርት እና አሜሪካ ሃገር የመኖሪያን ወጪ መሸፈኛ አቅሙ ካለ እና የተማሪ ቪዛ ለማግኘት የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ማሟላት ከተቻለ አሜሪካን አገር መጥቶ መማር ይቻላል። የ F-1 ቪዛ ለቋንቋ እና ለቀለም ትምህርት ሲሆን የኤም-1 ቪዛ ለሙያ ትምህርት ነው።
ተማሪ ቪዛ ለማግኘት የሚወሰዱ እርምጃዎች ምንድን ናቸው?
- የተማሪዎች እና ኤክስቼንጅ ጎብኚዎች ፕሮግራም ውስጥ የተካተተ በአሜሪካ የሚገኝ ትምህርት ቤት ማመልከት እና ተቀባይነት ማግኘት
- ፎርም I-20 (የተማሪ ቪዛ ለማግኘት ብቃት እንዳለ የሚገልጽ) ከትምህርት ቤቱ ማግኘት
- በ SEVIS ፕሮግራም መመዝገብ እና የ I-901 ክፍያ ፈጽሞ ደረሰኙን ማተም
- ፓስፖርት ማውጣት
- የደርሶ መልስ የቪዛ ማመልከቻ ፎርም (DS-160) መሙላት እና የማረጋገጫ ገጹን ማተም
- የማይመለስ የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ መክፈል
- የቪዛ ቃለ መጠይቅ በአዲስ አበባ አሜሪካን ኤምባሲ ማድረግ
- ቪዛ ማግኘት
- ወደ አሜሪካ ለመምጣት የጉዞ እቅድ ማውጣት