ቢ-2 ቪዛ
- ለቱሪዝም
- ለእረፍት
- ዘመድ ወይም ወዳጅ ጥየቃ
- ለህክምና
- ክፍያ ሳይቀበሉ በሙዚቃ፣ በስፖርት ወይም በውድድር ላይ ለመሳተፍ
- አጫጭር የመዝናኛ ኮርሶች ለመካፈል
ቢ-1 ቪዛ
ቢ1 ቪዛ ያላቸው ሰዎች በሚከተሉት እንቅስቃሴዎች መሳተፍ ይችላሉ፦
- ከአሜሪካን ውጭ የሚመረቱ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ እንዲሁም የሸቀጦች ትእዛዝ ለመውሰድ።
- የሚያወጡትን ገንዘብ ብቻ የሚሸፍን ንግግር ለማድረግ።
- ሳይንሳዊ፥ ትምህርታዊ፥ የሙያ፥ ወይም የንግድ ስብሰባ ለመሳተፍ።
- በፕሮፌሽናል አትሌት ደረጃ ለሽልማት ገንዘብ ለመወዳደር።
- እውቅና ያለው የሃይማኖት ወይም የበጎ አድራጎት ድርጅት አባል ሆነው የአሜሪካ ነዋሪዎችን ለመጥቀም ፈቃደኛ ሠራተኛ ሆኖ ለመምጣት።
የቪዛ ማመልከቻ የሚደግፉ ሰነዶች
- የቤተሰብ፣ የሥራ፣ የንብረት፣ የሀይማኖት ትስስር ምክንያት ከቆይታ በኋላ ወደ ሃገር እንደሚመለሱ የሚያሳይ ማስረጃ።
- አሜሪካ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ።
የህክምና ቪዛ ለመጠየቅ
- የበሽታው ምንነትና በአሜሪካ ውስጥ ሕክምና የሚያስፈልግበትን ምክንያት የሚያብራራ የሕክምና ማስረጃ።
- በአሜሪካ ከሚገኝ አንድ ሐኪም ወይም የሕክምና ተቋም የተላከ ሕክምናው ምን ያህል ርዝመትና ወጪ እንደሚጠይቅ የሚገልጽ ደብዳቤ (የዶክተሮችን ክፍያ፣ የሆስፒታል ክፍያ እንዲሁም ከሕክምና ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ጨምሮ) ።
- የታካሚው መጓጓዣ እና የሕክምና ወጪ ለመክፈል አቅም እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ።