- የ DS-160 ኦንላይን የደርሶ መልስ ቪዛ ማመልከቻ ሞልተው የማረጋገጫ ገጹን ያትሙ። ፎርሙን እዚ ያገኛሉ https://ceac.state.gov/GenNIV/ በከፊል የተጠናቀቀ የ DS-160 ቅጽ አቋርጠው መውጣት እና በ 30 ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ መመለስ ይችላሉ።
- ቪዛውን ይክፈሉ እና በአሜሪካ ኤምባሲ ለቃለ መጠይቅዎ ቀጠሮ ያስይዙ ለቪዛ መክፈል
DS-160ን ሲሞሉ የሚከተሉት ሰነዶች ያስፈልጎታል፦
- ፓስፖርት
- ወደ አሜሪካ ለመጨረሻ 5 ጊዚያት የተጓዙባቸው ቀናቶች (የሚመለከቶት ከሆነ)
- የትምህርት እና የስራ ሰነዶች
- የተማሪዎች እና ልውውጥ ጎብኚዎች የI-20 ወይም DS-2019 ቅጽ
- በአቤቱታ ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ ሰራተኞች የI-129 ቅጽ
ለቃለ-መጠይቁ የሚከተሉትን ይዛችሁ ይምጡ፦
- በአሜሪካ ከሚያረጉት ቆይታ ጊዚያት ውጪ ቢያንስ ለስድስት ወራት የሚያገለግል ፓስፖርት።
- የአሜሪካ የመጨረሻ ጊዜ ቪዛ የታተመበት ፓስፖርት (ከዚህ በፊት ተጉዘው ከሆነ)
- የደርሶ መልስ ቪዛ ማመልከቻ ቅጽ Form DS-160 የማረጋገጫ ገጽ።
- ከሚከተለው ድረ ገጽ የታተመ የማረጋገጫ እና መመሪያ ገጽ https://ais.usvisa-info.com/en-et/niv/users/sign_in
- ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተነሱት አንድ 5 x 5 ሴሜ (ወይም 2 x 2 ኢንች) የቀለም ፎቶግራፍ።
- ተጓዥ የቤተሰብ አባላት ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የልደት የምሥክር ወረቀት ለባል ወይም ለሚስት ደግሞ የጋብቻ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ።
ለተለያዩ የቪዛ መደቦች የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ሰነዶች
በተጨማሪም የተለያዩ የቪዛ መደቦች ተጨማሪ ሰነዶች ይጠይቃሉ፦