- ዋንኛው ምክንያት ከጉብኝት በኋላ ወደ ሃገሮት እንደሚመለሱ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ከለጎደለ ነው። አንዳንድ ድጋፍ ሰጪ ሰነዶች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ
- ከሥራ ቦታ ምን እንደሚሰሩ ፤ ለምን ያህል ጊዜ እንደሰሩ ፤ እና ምን ያህል እንደሚከፈል የሚገልጽ ደብዳቤ
- ከሃይማኖት ድርጅት አባል እንደሆኑና በምን መልኩ እንደሚያገለግሉ የሚገልጽ ደብዳቤ
- የንብረት ወይም የንግድ ማስረጃ
- የባንክ ሒሳብ እና ሌሎች የገንዘብ ሰነዶች
- አሁን እየተማሩ እንደሆነ የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ
- ሌላው ምክንያት ለጉዞ እና በአሜሪካ ለሚያረጉት ቆይታ በቂ ገንዘብ እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረቡ ነው። በተቀማጭ ገንዘብ መክፈል እንደሚችሉ ማሳየት ይችላሉ ። ወይም ደግሞ ሌላ ሰው ቆይታዎን እንዲደጉም (ስፖንሰር) መጠየቅ ይችላሉ። ስፖንሰር የሚያደርጎት ሰው ፎርም I-134ን መጠቀም ይችላል። ያለፈው ዓመት የግብር ክፍያ ማስረጃ፣ የገቢ ማረጋገጫ እና የንብረቶችን ማስረጃ የወራዊ የባንክ ሂሳብ፣ የኢንቨስትመንት ሂሳብ፣ ቦንድ፣ እና የቤታቸውን ዋጋ ኮፒ እንደግጋፋዊ መረጃ ማቅረብ ይችላሉ።
- የጉዞ እቅድዎን በተመለከተ ግልጽ የሆነ መረጃ ባለመቅረቡ። የት እንደሚቆዩ ፥ እስከ መቼ ፥ ለምን እንደሚጓዙ ለምሳሌ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት፣ ቤተሰብ ወይም ወዳጅ ለመጠየቅ የመሳሰሉት። የጉዞ ዓላማ በተቻለ መጠን በዝርዝር ያስረዱ።
- ባለፈው ጊዜ አሜሪካ በተደረገ ቆይታ I-94 ላይ ከተፈቀደው ጊዜ በላይ በመቆየት። ይህ ደግሞ በሚቀጥለው ጊዜ ቪዛ ለማግኘት ወይም ወደ አሜሪካ ለመግባት ችግር ሊያመጣ ይችላል።
- ቪዛው የተከለከለበት ምክንያት ሳይለወጥ ዳግም ማመልከቻ ማስገባት።
- ቪዛውን አብዛኛውን ጊዜ አሜሪካ ለመቆየት ከተጠቀሙበት። ይህም ወደ አሜሪካ ለመሰደድ ዓላማ እንዳሎዎት ይጠቁማል።
- ቪዛ ለማግኘት ሐሰትኛ መረጃ ማቅረብ። የምናስገባቸው መርጃዎች ወደፊትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለሚታዩ ከነሱ ጋር የሚገናኝ ማንኛውም የስደተኛ ጉዳይ ሊያበላሽ ይችላል።