ለስደተኛ ቪዛ ለማመልከት

  1. ዘመድዎ የአሜሪካን የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS) ፎርም I-130 ን በመጠቀም ከእርስዎ ጋር ያላቸውን ቤተስባዊ ግንኙነት መሰረት በማድረግ ለስደተኛ ቪዛ እንዲሰጥዎት ማመልከቻ ያቀርባሉ።
  2. የብሔራዊ ቪዛ ማእከል ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ የእርስዎን ጉዳይ ቁጥር እና የመታወቂያ ቁጥር የያዘ ኢ-ሜይል ወይም ደብዳቤ ይልክልዎታል። የማመልከቻውን ሂደት ወደፊት ለመግፋት እነዚህ ቁጥሮች ያስፈልጉዎታል። የእርስዎ አቤቱታ የቀረበበት ቀን የእርስዎ ቅድሚያ (ፕራዮሪቲ) ቀን ይባላል። የስደተኞች ቪዛ የሚሰጠው በወረፋ ነው። የብሔራዊ ቪዛ ማእከል በአሁኑ ጊዜ ላይ የሚያስተናግዳቸውን ቅድሚያ (ፕራዮሪቲ) ቀናት እዚ ማጣራት ይችላሉ https://travel.state.gov/content/travel/en/legal/visa-law0/visa-bulletin.html የሚስተናገዱበት ቀን ከደረሰ በሓላ፡
    • የስደተኛ ቪዛ ሂደት ማመልከቻ ክፍያ መክፈል ይኖርብዎታል።
    • የድጋፍ (ስፖንሰር) ክፍያን መክፈል ይኖርብዎታል።
    • ክፍያ ገንዘብ በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኝ ባንክ እንዲዛወር ይጠይቃል።
    • እዚ ገጵ ላይ ሁለቱንም ክፍያዎች በተናጠል መክፈል የችላሉ https://ceac.state.gov/IV/Login.aspx
    • የክፍያዎን ሁኔታ በድረ-ገፁ ላይ ማጣራት ይችላሉ። የስደተኛ ቪዛ ማመልከቻ ቅጽ DS-260 ን ከመሙላትዎ በፊት ክፍያው እንዲጠናቀቅ አንድ ሳምንት ገደማ ይፈጃል።
  3. የስደተኞች ቪዛ ማመልከቻ ቅጽ DS-260 ይሞላሉ። ለአሜሪካን ኤምባሲ የቪዛ ቃለ-መጠይቅዎ ለማቅረብ የማረጋገጫ ገጹን ያትሙ።
  4. ሁሉንም ድጋፍ ሰጪ ሰነዶች ለNVC እንዲላኩ ይጠየቃሉ። ሁሉም አስፈላጊ ሰነዶች ከተጠናቀሩ በኋላ ጉዳዮትን አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ለቃለ መጠይቅ ያስተላለፋል።
    • በአጠቃላይ የእርስዎ ስፖንሰር የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ አለበት
      • በቅርብ ጊዜ የ 3 ዓመታት አይአርኤስ የግብር መረጆች
      • የገቢ ማረጋገጫ (W2)
      • የቅርብ ጊዜ የባንክ እና የኢንቨስትመንት መግለጫዎች
      • የማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የስፖንሰርዎ ገቢ መግለጫ
      • የንብረቶች ዝርዝር
    • ከእርስዎ ጋር ያለውን ዝምድና ማስረጃ
    • ስፖንሰርዎ በአሜሪካን የመኖርያቸው ማስረጃ
    • የእርስዎ ስፖንሰር የኢሚግረሽን ሁኔታ ማረጋገጫ (የአሜሪካን ዜጋ ወይም የህጋዊ ኗሪነት ማረጋግጫ)
  5. ሌሎች ሰነዶችን ማዘጋጀት አለብዎት
    • የኦሪጂናል የልደት የምስክር ወረቀት፣ የአማርኛ ትርጉም እና ኮፒ
    • የጋብቻ የምሥክር ወረቀት (የሚመለከቶት ከሆነ)፣ የእንግሊዝኛ ትርጉም እና ኮፒ
    • የፍቺ የምሥክር ወረቀት (የሚመለከቶት ከሆነ)፣ የእንግሊዝኛ ትርጉም እና ኮፒ
    • የሞት የምሥክር ወረቀት (የሚመለከቶት ከሆነ)፣ የእንግሊዝኛ ትርጉም እና ኮፒ
    • ሕጋዊ መታወቂያ እና ኮፒ
    • ለማንኛውም 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ሰው የፖሊስ ምስክር ወረቀት
  6. ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉበትን ቀንና ሰዓት ከአሜሪካን ኤምባሲ ቀጠሮ ካገኙ በኋላ ሕክምና ምርመራ ማድረግ ከተፈቀደላቸው የህክምና ተቋማት መካከል አንዱ ጋር ምርመራ ለማድረግ ቀጠሮ ይያዙ። ይህን ሂደት ከጨረሱ በኋላ ወደ ቪዛ ቃለ መጠይቅዎ ማምጣት ያለብዎት የታሸገ ፖስታ ይሰጦታል። ወደ ህክምና ምርመራ የሚከተሉትን ሰነዶች መውሰድ ያስፈልግዎታል
    • የቪዛ ቃለ መጠይቅ የቀጠሮ ደብዳቤ
    • ፓስፖርት
    • ስድስት (6) በቅርቡ የተነሱት የፓስፖርት ፎቶ እና
    • የክትባት ወረቀት
  7. ለቪዛ ቃለ መጠይቅ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
    • የብሔራዊ ቪዛ ማእከል ለቃለመጠይቅ የላከውን ደብዳቤ ኮፒ (ለዲቪ ቪዛ፣ ለእጮኛ፣ ለጉዲፈቻ ወይም ለስደተኛ አመልካቾች አያስፈልግም)
    • ከታሰበው ጉዞ ቀን በሓላ ቢያንስ ለ6 ወራት የሚያገለግል ፓስፖርት
    • የእያንዳንዱ ሰው ሁለት (2) ፎቶ (5 ሴሜ x 5 ሴሜ)
    • በኢንተርኔት የተሞላው የስደተኛ ቪዛ ማመልከቻ ፎርም DS-260 የታተመው የማረጋገጫ ገጽ
    • ከላይ ከቁጥር 4 እና 5 በታች የተዘረዘሩት ሌሎች ሰነዶች።
  8. የቪዛ ማመልከቻው ሲጸድቅ በፓስፖርትዎ ላይ ማኅተም ይደረግበታል። በቪዛው ላይ ያለው መረጃ በሙሉ በፓስፖርቶት ላይ ካለው መረጃ ጋር ልክ መሆኑን አረጋግጡ። ካልሆነ ወደ አሜሪካን ኤምባሲ እንዲስተካከል መልሰው ያምጡት። በተጨማሪም ኤምባሲው ለመጀመሪያ ጊዜ አሜሪካን ሲደርሱ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ለኢሚግሬሽን ባለ ሥልጣናት መስጠት ያለቦትን ሰነዶች የያዘ የታሸገ ፖስታ ይሰጦታል። የሕክምና ምርመራ በሚያደርጉበት ጊዜ ኤክስሬይ ከተነሱ የኤክስሬዩን ፊልም አብረው ከታሸገው ፖስታ ጋር ለኢሚግሬሽን ባለ ሥልጣኑ ይስጡ።
  9. የእርስዎ ፎርም I-551 (ግሪን ካርድ) በቪዛ ማመልከቻ ቅጽዎ ውስጥ ወደ ሞሉት የአሜሪካን አድራሻ ይላካል።
  10. ቪዛው ከማለቁ በፊት ወደ አሜሪካን መግባት አለቦት። ቪዛ አብዛኛውን ጊዜ የሚታተመው ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለስድስት ወር እንዲያገለግል ተደርጎ ነው።