ለቪዛ ለመክፈል

ለቪዛዎ ለመክፈል እና አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የቃለመጠይቅ ቀጠሮ ለመያዝ

ወደ https://ais.usvisa-info.com/am-et/niv ገጽ ያምሩ

  • የተጠቃሚ አካውንት ይክፈቱ
  • ቪዛ ለማግኘት የሚያመለክት እያንዳንዱ ሰው የ DS-160 ማረጋገጫ ቁጥር ያስገባ
  • የ “ኮሪየር ሰነድ ተመላሽ” ሂደትን ይጨርሱ
  • ለሚያመለክቱት የቪዛ አይነት የማመልከቻ ክፍያ ይክፈሉ። በጥሬ ገንዘብ የሚለውን ይምረጡ እና መመሪያውን ይከተሉ።
  • የኤምባሲ የቪዛ ቃለመጠይቅ ቀጠሮ ይያዙ

የጥሬ ገንዘብ ክፍያ ማስታወሻዎች

የገንዘብ ክፍያው እንዲጠናቀቅ እና በሲስተሙ ውስጥ እንዲገባ ሁለት የሥራ ቀናት ይጠብቁ። ከአንድ ጊዜ በላይም እንዳይከፈሉ።

ከቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ጋር በተያያዘ ለሚያጋጥሙ ጉዳዮች

በአዲስ አበባ የሚገኙትን አሜሪካ ኤምባሲ ቆንስላ ክፍል በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ያነጋግሩ weeac_contactus+et+mrv+en@visaops.net

የቪዛ ቃለ-መጠይቅ ቀጠሮ ምን ያህል ያስጠብቃል?

ለተለያዩ የቪዛ ዓይነቶች የኤምባሲ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ቀጠሮ ለማግኘት ምን ያህል እንደሚያስጠብቅ ለማየት ይሕን ሊንክ መጎብኘት ይችላሉ።

የቪዛ ማመልከቻ ሁኔታ ለማየት

https://ceac.state.gov/CEAC/ ይጎብኙ

የቀጠሮ ቀን ለመቀየር

https://ais.usvisa-info.com/am-et/niv ገጽ ላይ በመግባት ያለተጨማሪ ክፍያ የቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ መስረዝ እና እንደገና ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ የጥሪ ማዕከል ቁጥር

+251115582424

ስለ ቪዛ ክፍያዎች ማወቅ ያለብን ነገሮች

  • የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ የማይመለስ ነው
  • የአንድ ሰውን የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ሌላ ሰው ሊጠቀምበት አይችልም
  • ቪዛ ከተከለከሉና እንደገና ማመልከት ከፈለጉ እንደገና መክፈል ይኖርቦታል።
  • የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ከተደረገበት ቀን አንስቶ ለ365 ቀናት ያገለግላል።
  • በአንድ አገር የተከፈለ የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ሌላ አገር መጠቀም አይቻልም።

የአሜሪካን የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ

የደርሶ መልስ ቪዛ ክፍያዎች

  • ለንግድ ወይም ለቱሪዝም ፥ ተማሪዎች እና ተለዋዋወጫ ጎብኚዎች $ 185 ዶላር ነው።
  • ለጊዜያዊ ሠራተኞች (H, L, O, P, Q, እና R ምድቦች) $ 205 ዶላር ነው።
  • በልዩ ልዩ ሙያ (E ምድብ) ውስጥ ለስምምነት ነጋዴዎች፣ ለስምምነት ኢንቨስተሮችና ለስምምነት አመልካቾች $315 ዶላር ነው።

የስደተኛ ቪዛ ክፍያዎች

  • ለስደተኛ ቪዛ ክፍያው $325 ዶላር ነው። በቃለ መጠይቁ ላይ ይህን ገንዘብ በድጋፍ ሰጪዎ (ስፖንሰር መሚያደርጎት) ሰው ካልተከፈለ በአካል መክፈል ይችላሉ።
  • ለዲቪ ቪዛ ክፍያው $330 ዶላር ነው። ቃለ መጠይቅ በሚያደርጉበት ጊዜ ይህን ገንዘብ በአካል መክፈል ይችላሉ።