ቪዛ

ወደ አሜሪካ መጓዝ የሚፈልጉ መንገደኞች በሙሉ ቪዛ ያስፈልጋቸዋል። ስደተኛ ቪዛ እዛ ለዘለቄታው መኖር ለሚፈልጉ ሰዎች ሲሆን ስደተኛ ያልሆነ ቪዛ ደግሞ ወደ አገራቸው ለመመለስ ላሰቡ ሰዎች ነው።

  • የቪዛ ማመልከቻ ሂደቱ ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል ሂደቱን ቀደም ብሎ መጀመር ይመከራል። 
  • በተጨማሪም ቪዛ ሊከለከል ስለሚችል ጥብቅ የጉዞ እቅድ አያድርጉ። 
  • ቪዛው ያልተመታበት ምክንያት ከተፈታ እንደገና የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ከፍለው ለሌላ ቪዛ ማመልከት ይችላሉ።
  • ቪዛው የተመታበት ፓስፖርት አገልግሎት ቀን ካለፈ አዲስ ፓስፖርት አውጥተው ሁለቱንም ፓስፖርት ይዘው መጓዝ የችላሉ።