የቪዛ ፎቶ መስፈርቶች

የፎቶግራፍ መስፈርቶች

  1. ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የተነሱት ፎቶ
  2. በነጭ ባክግራውንድ ላይ
  3. ፊት ሙሉ በሙሉ መታየት አለበት
  4. በየዕለቱ የሚለብሱትን ልብስ ይልበሱ። ዩኒፎርም ለብሶ መነሳት አይፈቀድም።
  5. በሃይማኖት ምክንያት እና እለት እለት የሚያረጉት ካልሆነ በስተቀር ባርኔጣ ወይም ራስ መሸፈኛ አያድርጉ። ካረጉም ፊቶት ላይ ምንም ዓይነት ጥላ መጣል የለበትም።
  6. መነጽር አድርጎ ፎቶ መነሳት አይፈቀድም። መነጽር አድርገው ከተነሱ የሕክምና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርቦታል። የሌንስ ፍሬም ወይም ነጸብራቅ ዓይኖትን ሊሸፍን አይገባም።

የታተመ ፎቶ

  1. የግድ 51 ሚሊ ሜትር በ 51 ሚሊ ሜትር መሆን አለበት
  2. ከራስ እስከ አገጭ በቁመት 25 ሚሊ ሜትር – 35 ሚሊ ሜትር መሆን ይኖርበታል
  3. የዓይን ቁመት (ከምስሉ ታች እስከ ዓይን ድረስ ሲለካ) ከ28 ሚሜ – 35 ሚሊ ሜትር መሆኑን ያረጋግጡ

ዲጂታል ፎቶ

  1. ፀጉሩን ጨምሮ ከራስ እስከ ታችኛው የአገጭ ክፍል ከ 50% እስከ 69% የምስሉ ጠቅላላ ቁመት መሆን አለበት።
  2. የዓይን ቁመት (ከምስሉ ታች እስከ ዓይን ድረስ ሲለካ) የምስሉ ቁመት ከ56% እስከ 69% መሆን ይኖርበታል።
  3. የምስል ፒክስል ስፋት በአንድ ካሬ ገጽታ ውስጥ መሆን አለበት (ማለት ቁመቱ ከስፋቱ ጋር እኩል መሆን አለበት ማለት ነው)። ከ 600 ፒክስል (ስፋት) x 600 ፒክስል (ቁመት) እስከ 1200 ፒክስል (ስፋት) x 1200 ፒክስል (ቁመት) ናቸው ተቀባይነት አለው።
  4. የፋይሉ መጠን 240 KB ወይም ከዚያ በታች መሆን አለበት።
  5. የፋይል ቅርጸት jpg ወይም jpeg እና በ SRGB ቀለም ቦታ መሆን አለበት።