የንግድ ወይም የጉብኝት ቪዛ (ቢ-1/ቢ-2)

ቢ-2 ቪዛ

  1. ለቱሪዝም
  2. ለእረፍት
  3. ዘመድ ወይም ወዳጅ ጥየቃ
  4. ለህክምና
  5. ክፍያ ሳይቀበሉ በሙዚቃ፣ በስፖርት ወይም በውድድር ላይ ለመሳተፍ
  6. አጫጭር የመዝናኛ ኮርሶች ለመካፈል

ቢ-1 ቪዛ

ቢ1 ቪዛ ያላቸው ሰዎች በሚከተሉት እንቅስቃሴዎች መሳተፍ ይችላሉ፦

  1. ከአሜሪካን ውጭ የሚመረቱ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ እንዲሁም የሸቀጦች ትእዛዝ ለመውሰድ።
  2. የሚያወጡትን ገንዘብ ብቻ የሚሸፍን ንግግር ለማድረግ።
  3. ሳይንሳዊ፥ ትምህርታዊ፥ የሙያ፥ ወይም የንግድ ስብሰባ ለመሳተፍ።
  4. በፕሮፌሽናል አትሌት ደረጃ ለሽልማት ገንዘብ ለመወዳደር።
  5. እውቅና ያለው የሃይማኖት ወይም የበጎ አድራጎት ድርጅት አባል ሆነው የአሜሪካ ነዋሪዎችን ለመጥቀም ፈቃደኛ ሠራተኛ ሆኖ ለመምጣት።

የቪዛ ማመልከቻ የሚደግፉ ሰነዶች

  • የቤተሰብ፣ የሥራ፣ የንብረት፣ የሀይማኖት ትስስር ምክንያት ከቆይታ በኋላ ወደ ሃገር እንደሚመለሱ የሚያሳይ ማስረጃ።
  • አሜሪካ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ።

የህክምና ቪዛ ለመጠየቅ

  • የበሽታው ምንነትና በአሜሪካ ውስጥ ሕክምና የሚያስፈልግበትን ምክንያት የሚያብራራ የሕክምና ማስረጃ።
  • በአሜሪካ ከሚገኝ አንድ ሐኪም ወይም የሕክምና ተቋም የተላከ ሕክምናው ምን ያህል ርዝመትና ወጪ እንደሚጠይቅ የሚገልጽ ደብዳቤ (የዶክተሮችን ክፍያ፣ የሆስፒታል ክፍያ እንዲሁም ከሕክምና ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ጨምሮ) ።
  • የታካሚው መጓጓዣ እና የሕክምና ወጪ ለመክፈል አቅም እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ።