የደርሶ መልስ ቪዛ የሚከለከሉበት አንዳንድ ምክንያቶች

  1. ዋንኛው ምክንያት ከጉብኝት በኋላ ወደ ሃገሮት እንደሚመለሱ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ከለጎደለ ነው። አንዳንድ ድጋፍ ሰጪ ሰነዶች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ
    • ከሥራ ቦታ ምን እንደሚሰሩ ፤ ለምን ያህል ጊዜ እንደሰሩ ፤ እና ምን ያህል እንደሚከፈል የሚገልጽ ደብዳቤ
    • ከሃይማኖት ድርጅት አባል እንደሆኑና በምን መልኩ እንደሚያገለግሉ የሚገልጽ ደብዳቤ
    • የንብረት ወይም የንግድ ማስረጃ
    • የባንክ ሒሳብ እና ሌሎች የገንዘብ ሰነዶች
    • አሁን እየተማሩ እንደሆነ የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ
  2. ሌላው ምክንያት ለጉዞ እና በአሜሪካ ለሚያረጉት ቆይታ በቂ ገንዘብ እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረቡ ነው። በተቀማጭ ገንዘብ መክፈል እንደሚችሉ ማሳየት ይችላሉ ። ወይም ደግሞ ሌላ ሰው ቆይታዎን እንዲደጉም (ስፖንሰር) መጠየቅ ይችላሉ። ስፖንሰር የሚያደርጎት ሰው ፎርም I-134ን መጠቀም ይችላል። ያለፈው ዓመት የግብር ክፍያ ማስረጃ፣ የገቢ ማረጋገጫ እና የንብረቶችን ማስረጃ የወራዊ የባንክ ሂሳብ፣ የኢንቨስትመንት ሂሳብ፣ ቦንድ፣ እና የቤታቸውን ዋጋ ኮፒ እንደግጋፋዊ መረጃ ማቅረብ ይችላሉ።
  3. የጉዞ እቅድዎን በተመለከተ ግልጽ የሆነ መረጃ ባለመቅረቡ። የት እንደሚቆዩ ፥ እስከ መቼ ፥ ለምን እንደሚጓዙ ለምሳሌ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት፣ ቤተሰብ ወይም ወዳጅ ለመጠየቅ የመሳሰሉት። የጉዞ ዓላማ በተቻለ መጠን በዝርዝር ያስረዱ።
  4. ባለፈው ጊዜ አሜሪካ በተደረገ ቆይታ I-94 ላይ ከተፈቀደው ጊዜ በላይ በመቆየት። ይህ ደግሞ በሚቀጥለው ጊዜ ቪዛ ለማግኘት ወይም ወደ አሜሪካ ለመግባት ችግር ሊያመጣ ይችላል።
  5. ቪዛው የተከለከለበት ምክንያት ሳይለወጥ ዳግም ማመልከቻ ማስገባት።
  6. ቪዛውን አብዛኛውን ጊዜ አሜሪካ ለመቆየት ከተጠቀሙበት። ይህም ወደ አሜሪካ ለመሰደድ ዓላማ እንዳሎዎት ይጠቁማል።
  7. ቪዛ ለማግኘት ሐሰትኛ መረጃ ማቅረብ። የምናስገባቸው መርጃዎች ወደፊትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለሚታዩ ከነሱ ጋር የሚገናኝ ማንኛውም የስደተኛ ጉዳይ ሊያበላሽ ይችላል።