ጥገኝነት

ጥገኝነት ለመጠየቅ

በዘር፣ በሃይማኖት፣ በብሔር፣ በአንድ የተወሰነ ማኅበራዊ ቡድን አባልነት ወይም በፖለቲካዊ አመለካከት ምክንያት ስደት እንደደረሰ ወይም እንደሚደርስ ፍራቻ እንዳለ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ከተቻለ ጥገኝነት መጠየቅ ይቻላል።

ጥገኝነት ለማመልከት ቅጽ I-589, Application for Asylum and for Withholding of Removal ወደ አሜሪካን ከተገባ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያለ ክፍያ ማስገባት ይቻላል።

ማመልከቻውን ከሚያስገቡበት ጊዜ አንስቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚወሰንበት ጊዜ ድረስ በአሜሪካ የሚገኙ የትዳር አጋርና ልጆች ማመልከቻው ላይ ሊያካትቱ ይችላሉ። ልጆችን በማመልከቻው ላይ ለማካተት ከ21 ዓመት በታችና ያላገቡ መሆን አለባቸው።

የስራ ፈቃድ

የጥገኝነት ፈቃድ ማመልከቻው ተቀባይነት ሲያገኝ የስራ ፈቃድ ማመልከት ይቻላል። ሆኖም የጥገኝነት ፈቃድ (ባመልካች ከተከሰተ መጓተት ውጪ) ምንም አይነት ውሳኔ ሳይወሰን 150 ቀናት ካለፉ የስራ ፈቃድ መጠየቅ ይቻላል።

የስራ ፈቃድ ለማግኘት ፎርም I-765, Application for Employment Authorization ማስገባት ያስፈልጋል። የጥገኝነት ማመልከቻ ከገባ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቀርብ የስራ ፈቃድ ማመልከቻ ክፍያ የለውም።

ቤተሰብ ለማምጣት

የጥገኝነት ፈቃድ ከተስጠ በኋላ የትዳር አጋር እና ልጆችን ፎርም Form I-730, Refugee/Asylee Relative Petition በማቅረብ ወደ አሜሪካ እንዲመጡ አቤቱታ ማስገባት ይቻላል። ልጆች ከ21 ዓመት በታች እና ያላገቡ መሆን አለባቸው ።

ሰብዓዊ ምክንያቶች ካልኖሩ በስተቀር ጥገኝነት ከተገኘ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የI-730 አቤቱታ መቅረብ አለበት። ምንም ክፍያ አይጠይቅም።

ለህጋዊ መኖሪያ (ግሪን ካርድ) ማመልከት

የጥገኝነት ፈቃድ ከተገኘ አንድ ዓመት በኋላ ለግሪን ካርድ ቅጽ I-485, Application to Register Permanent Residence, or to Adjust Status በማስገባት ማመልከት ይቻላል። ግሪን ካርድ ያገኘው ሰው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ግሪን ካርድ ማመልከት አለበት።