የደርሶ መልስ ቪዛ ለማመልከት

  1. የ DS-160 ኦንላይን የደርሶ መልስ ቪዛ ማመልከቻ ሞልተው የማረጋገጫ ገጹን ያትሙ። ፎርሙን እዚ ያገኛሉ https://ceac.state.gov/GenNIV/ በከፊል የተጠናቀቀ የ DS-160 ቅጽ አቋርጠው መውጣት እና በ 30 ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ መመለስ ይችላሉ።
  2. ቪዛውን ይክፈሉ እና በአሜሪካ ኤምባሲ ለቃለ መጠይቅዎ ቀጠሮ ያስይዙ ለቪዛ መክፈል

DS-160ን ሲሞሉ የሚከተሉት ሰነዶች ያስፈልጎታል፦

  • ፓስፖርት
  • ወደ አሜሪካ ለመጨረሻ 5 ጊዚያት የተጓዙባቸው ቀናቶች (የሚመለከቶት ከሆነ)
  • የትምህርት እና የስራ ሰነዶች
  • የተማሪዎች እና ልውውጥ ጎብኚዎች የI-20 ወይም DS-2019 ቅጽ
  • በአቤቱታ ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ ሰራተኞች የI-129 ቅጽ

ለቃለ-መጠይቁ የሚከተሉትን ይዛችሁ ይምጡ፦

  • በአሜሪካ ከሚያረጉት ቆይታ ጊዚያት ውጪ ቢያንስ ለስድስት ወራት የሚያገለግል ፓስፖርት።
  • የአሜሪካ የመጨረሻ ጊዜ ቪዛ የታተመበት ፓስፖርት (ከዚህ በፊት ተጉዘው ከሆነ)
  • የደርሶ መልስ ቪዛ ማመልከቻ ቅጽ Form DS-160 የማረጋገጫ ገጽ።
  • ከሚከተለው ድረ ገጽ የታተመ የማረጋገጫ እና መመሪያ ገጽ https://ais.usvisa-info.com/en-et/niv/users/sign_in
  • ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተነሱት አንድ 5 x 5 ሴሜ (ወይም 2 x 2 ኢንች) የቀለም ፎቶግራፍ።
  • ተጓዥ የቤተሰብ አባላት ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የልደት የምሥክር ወረቀት ለባል ወይም ለሚስት ደግሞ የጋብቻ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ።

ለተለያዩ የቪዛ መደቦች የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ሰነዶች

በተጨማሪም የተለያዩ የቪዛ መደቦች ተጨማሪ ሰነዶች ይጠይቃሉ፦